ጅግጅጋ ጥቅምት ፰ ቀን ፳፼፲፬ (የኢት.ድ) የሱማሌ ክልላዊ መንግስት መስራች ጉባኤ አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድን የክልሉ ርዕሰ መስተደድር ሆነው እንዲመሩ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ።
አቶ ሙስጠፌ ባለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ የተገኘውን ሁለንተናዊ ለውጥ በብቃት መምራት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ መሆናቸው ተመልክቷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ህግን መሰረት በማድረግ የተጣለባቸውን ታላቅ መንግስታዊና ህዝባዊ ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት እንደሚፈፅሙ በምክር ቤቱ ጉባኤ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል ።
መንግስታቸውን ለማዋቀር የሚያስችላቸውን የካቢኔ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበው እንደሚያፀድቁ ይጠበቃል።
አሁን ላይ በቀጣይ አምስት ዓመታት በክልሉ ስለሚከናወኑ የልማት፣የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን አስመልክተው ንግግር እያደረጉ ይገኛል።
በመንግሥት ምስረታው ላይ የፌደራል እና የክልል እንዲሁም የተጎራባች ሀገራት ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።
አስተያየት ይለጥፉ