ቻይና ለታዳጊ አገራት ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ 233 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች

ጥቅምት ፰ ቀን ፳፼፲፬ (የኢት.ድ) ቻይና በታዳጊ አገራት የብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ የሚያስችል የ233 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች።

ውሳኔው ቻይና የመሬት ደህንነትን ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ያመላከተ መሆኑን ናይሮቢን መቀመጫ ያደረገው የአፍሪካ ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን አስታውቋል፡፡

ቻይና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) 15ኛው የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ኮንፈረንስ መድረክ (ኮፕ-15) ላይ ይፋ አድርጓል።

መድረኩ በደቡብ ምዕራብ ዩዋና ግዛት ዋና ከተማ ኩንሚንግ ተካሂዷል።“የቻይና እና የሌሎችም ባለድርሻዎች ድጋፍ ሃብት የማሰባሰብ የመጀመሪያው ስራ ሲሆን አመታዊ የብዝሃ ህይወት ኮንፈረንስን ተከትሎ አለም አቀፍ የብዝሃ ህይወት የገንዝብ አጥረትን የምንፈታበት አንዱ መላ ነው” ያሉት የፋውንዴሽኑ ስራ አስፈፃሚ ካድዩ ሴቢዩና በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

ቃል የተገባው የገንዘብ ድጋፍ የድህረ 2020 አለምአቀፍ የብዝሃ ህይወት አጀንዳንም ለመተግበር እንደሚያግዝ ነው የገለፁት ስራ አስፈፃሚው።

Post a Comment

أحدث أقدم